ሁላችንም ለመታሰር እንዘጋጅ!
ስርዓቱ ከትናትናው ዕለት ጀምሮ ሰላማዊ የፖለቲካ ታጋዮችን በጅምላ እያሰረ፤ እያጋዘ ይገኛል። እስከአሁን ባለው መረጃ ከአንድነት ሀላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ ከሰማያዊ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ ከአረና ደግሞ አቶ አብርሃ ደስታ መታሰራቸውን ተረጋግጠዋል። በመሆኑም ከዚህ በኋላ የፓርቲ ፖለቲካ ብቻ አይደለም የሚኖረው፤ ከዚህ በኋላ ትግሉ ለለውጥ የሚታገሉት በአንድ ጎራ፣ ስርዓቱ ደግሞ በሌላ ጎራ ተሆኖ ነው ትግሉ የሚካሄው። የትግል ጓደኞቻችን ወደ እስርቤት እየተጋዙ ነው፤ “ፍትህ እያሉ ቃሊቲ ይገቡ” እንደተባለው ከእንግዲህ እኛም ተከትለናቸው እንሄዳለን እንጂ ከቶ እነርሱ አሳስርን የምንተኛበት፤ ቁጭ ብለው ትርጉም የሌለው ኑሮ የምንገፋበት ሁኔታ አይኖርም። በምንም ተአምር እንደፊቱ አንዱ ሲታሰር ሌላው ዝም የሚልበት ሁኔታ የለም። ጓዶቻችን በፍፁም በእኛ አያፍሩም፤ በፍፅም ወኔ፣ በፍፁም ቆራጥነት እኛም ቃልቲ እንገባለን። እስር ማርከሻው እስር ብቻ ነው! የኢትዮጵያ ህዝብም ከእንግዲህ ልጆቹ አሳስሮ ተኝቶ ያድራል፤ እንቅልፍም ይወስደዋል ብዬ አለስብም፤ እንደዚያ ከሆነ እንደ ህዝብ ተሸንፈናል ማለት ነው። እንደ ህዝብ፣ እንደ ሀገር ከመሸነፍ ይሰውረን!

No comments:
Post a Comment