Friday, 15 August 2014

ወያኔ ሕወሓት

ወያኔ ሕወሓት በቅርቡ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ተጨመረ ብሎ በኢቲቪ ሲደሶኩርና ብሎም የተጨመረ ዶሞዝ ከእድገቱ የሚመጣጠን መሆኑን ኣፅንኦት ሰጥቶ ሲለፈልፍ ነበር የከረመው!!! እዉነቱ ግን የሓላ ሓላ ብቅ ብሎ የተጨመረ ዶሞዝ እንዳየነው ሲሆን ማፍያው ወያኔ በደሞዝ ጭማሪ ለይ የሚከተሉትን ኣራት ድራማዎች ኣሳይቶናል!!!
1. ዶሞዝ ጨመርኩኝ ብሎ ሲል ታክስ 35% ኣስገብቶ ከመንግስት ሰራተኛ ኪስ መዝረፍ ጀመረ ! የተጨመረው ደሞዝ የታክስ መጠኑ በማሳደግ ድሮ ከነበረው 32% ኣሁን 3% በመጨመር ምርጥ ድርማን ሰርቶዋል
2. ከሃገሪቱ ፈጣን እድገት የሚመጣጠን ነው እያለ ሲደሶኩር የከረመው ዝቅተኛ የደሞዝ ጭማሪ 200 ብር ሲሆን 4000 ይከፈል የነበረው ደግሞ በ33% ተባዝቶ ኣሁን 1320 ብር ጨምሮዋል!!! እዚጋ የሚታየው ጉዳይ በዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይና በደህና ተከፋይ የኑሮ ዉድነት ከማዛመት በስተቀር የደሞዝ ጭማሪው ለዜና መሳርያ ብቻ እንደሆነ ለማወቅ ወያኔ በቻ ኣለመሆን በቂ ነው ( ኮካዎች ቁጥር ፎብያ ስላላቸው ነው)!!!
3. ይህ የፈጣን እድገት የደሞዝ ጭማሪ የሃገሪቱ ነባራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ደረጃም ወያኔዎች ሳያቁት የት እንዳለንም ጭምር ኣሳይቶናል!!! በፈጣን እድገት ያለች ሃገር የደሞዝ ጭማሪ 200 ብር ስታደርግ እነ ሕወሓት ሓቁን ሳይታወቅባቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ ማሳየታቸው ህዝብ ማወቅ ችሎዋል!!!
4. መከረኛው ነጋዴ ንሮ ለማስወደድ በበርበሬ በዘይት በስካር ወዘተ የምግብ ኣገልግሎት የሚዉሉ እቃዎች ላይ ዋጋ ጨመራቹ ኣልጨመራችሁ እያለ የሌባና ፖሊስ ጨዋታ ወደ መጫወት ሰተት ብሎ ገብቶዋል!!!! ከዉሸት ወጥተው ኮካዎች የሃገሪቱ ትክክለኛ ኢኮኖሚ ማሳደግ እንደማይችሉት የሚያዉቁ ሕወሓቶች ዛሬ በነጋዴ ላይ መንግስትና ህዝብ ለመለያያት ወዘተ እያሉ በመከራ ኑሮዉን ለማሸነፍ እየተታገለ ላለው ህዝበ የስራ ቦታው ማሸግ እንደ መፍትሔ ተያይዞዉታል... ኣንጀትየ መንግስት!!!
ባጠቃለይ ሕወሓት እችን ሓገር ከመዝረፍ የዘለለ ፖሊሲ እንደሌለው 23 ዓመታት በሙሉ በዉሸት ስልጣን ላይ እንደኖረ ህዝባችን ኣዉቆ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ወያኔን ቀብረን በኢትዮጵያ ሃገራችን ባንዴራችንን ከፍ ኣድርገን የምንኖርባት ኢትዮጵያ እዉን ለመሆን 1 ዓመት ብቻ ቀርቶናል!!! (ግንቦት 2007 ዓም)
ነፃነት ቀርባለችና ... ወደ ሃላ ማየት የለም!!!!

No comments:

Post a Comment